የስራ ማስታወቂያ
ሚያዝያ 8 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ ኮንቲኔንታል የጤና አጠባበቅ ኢንስትቲዩት (አኮጤአኢ) በአዲስ አበባ ለሚያከናውነው ጥናት ከዚህ በታች ለተጠቀሰው ሥራ መደብ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመቅጠር ይፈልጋል።
የሥራ መደቡ፣ የምርምር ነርስ
ተፈላጊ መስፈርት፣
- የትምህርት ዝግጅት፣ በሚድዋይፈሪ/በነርሲንግ ዲግሪ ያላት በህፃናት እድገት ክትትል እና ምዘና ላይ የስራ ልምድ ያላት ቢሆን ይመረጣል ወይም እንደተጨማሪ ነጥብ ይያዛል፡፡
- ጾታ፡ ሴት
የቅጥሩ ዓይነት፣ የኮንትራት ቅጥር እንደአስፈላጊነቱ የሚታደስ
ደመወዝ፣ በኢንስቲትዩቱ የደመወዝ ስኬል መሠረት
የማመልከቻ ጊዜ፣ ከሚያዝያ 9 እስከ 24 ቀን 2ዐ18 ዓ.ም ሲሆን ተፈላጊውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ማመልከቻ ደብዳቤ፣ ሲቪ(CV) እና
የትምህርት ማስረጃችሁን በመያዝ በአካል በመቅረብ ማመልከት ወይም በኢሜል አድራሻ hraciph@gmail.com በመላክ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
በአካል የምታመለክቱ አመልካቾች በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2:30 እስከ 11፡00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2:30 እስከ 6:00 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 003 ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
ለመረጃ ስልክ 0955333339/0116-390000 መደወል የሚቻል መሆኑን እናሳውቃለን፡
